የካቲት 12 ቀን 1929



የኔፕልስ ልዕልት በመወለዷ ግራዚያኒ የደስታ መግለጫ ገንዘብ እሰጣለሁ ብሎ ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከድሮው ቤተመንግስት ድሆች እንዲሰበሰቡ አዘዘ።
1/9



የኔፕልስ ልዕልት በመወለዷ ግራዚያኒ የደስታ መግለጫ ገንዘብ እሰጣለሁ ብሎ ከዛሬው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከድሮው ቤተመንግስት ድሆች እንዲሰበሰቡ አዘዘ።
1/9
ከድሆቹ በስተቀር ታላላቅ የኢጣልያ ሹማምንት፣ የሜትሮፖሊታን ጳጳስ አቡነ ኪርልና ሌሎችም መኩአንንት ነበሩ። ለእያንዳንዱ ድሀም ሁለት ማርትሬዛ ብር እንዲሰጥ ተወስኖ ነበር። እኩለ ቀን ገደማ ላይ 3000 የሚሆኑ ድሆች ከቤተ መንግስቱ ገቡ።
2/9
2/9
ወዲያው በግቢው በር በኩል አንድ ቦምብ ፈነዳ። ቀጥሎም ሌላ ፈነዳ። ለሶስተኛ ጊዜ የተጣለው ቦምብ የፋሺስት ኢጣልያ መክዋንንት ካሉበት ቦታ ፈነዳ። ግራዚያኒ ጀርባውን ቆስሎ ወደቀ። በቀጠለው ጥቂት ደቂቃ ውስጥ ሌሎች ቦምቦች ተከታትለው ተጣሉ።
3/9
3/9
በጠቅላላው ግቢው ውስጥ ሰባት ቦምቦች ፈነዱ። ጄኔራል ሊታዩ የአዲስ አበባው ከንቲባ ጉይዶ ኮርቴሲ ጋዜጠኛው ማርዮ አፔሎስ እና ሌሎች 30 ያህል ሰዎች ቆሰሉ። የቦምቡ ፍንዳታ ጋብ እንዳለ አድፍጠው ተኝተው የነበሩ ወታደሮች ተነስተው ተኩስ ከፈቱ።
4/9
4/9
በዚያ ግቢ ውስጥ ያለማቁዓረጥ ሶስት ሰዓት ሙሉ ተኩስ ተካሄደ።ከጥቂት ጊዜ በህዋላ ባለ ጥቁር ሸሚዞች፣ የኢጣሊያ ሾፌሮች፣ የቅኝ ግዛት ወታደሮች በአዲስ አበባ ከተማ እየዞሩ ሕዝቡን ይፈጁት ጀመር።
5/9
5/9
በቁጥር 14154 ግራዚያኒ ሮማ ላለው ለቅኝ ግዛት ሚኒስቴር ባስተላለፈው ቴሌግራም "እነኚህ ጥቁሮች የኛን ወታደር ሲያዩ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ይላሉ። ይህን የሚሉትንም ለመቀጣጫ ሁሉንም አስጨረስክዋቸው። እደግመዋለሁ፣ አስጨረስክዋቸው" ብሏል።
6/9
6/9
የካቲት 12 ቀን በተጀመረው እልቂት በሶስት ቀን ውስጥ 30000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በህዋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እስር ቤቶች ተላከ።
7/9
7/9
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. ዛሬ ዩኒቨርሲቲ በሆነው ግቢ ውስጥ ቦምቦች ሲፈነዱ ቦምቦቹ የተጣሉት ከሁለት ይሁን ከብዙ ሰዎች እስካሁን የታወቀ መረጃ የለም ግራዚያኒ አጠገብ የፈነዳውን ግን አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም ጋር እንደጣሉት ይነገራል
8/9
8/9
ምንጭ: የኢትዮጵያ እና የኢጣልያ ጦርነት በጳውሎስ ኞኞ
ፎቶዎቹ ከተለያዩ ድረገፆች
ሙሉውን ታሪክ ለማግኘት
https://www.sewasew.com/phrases/5548?withDetails=
#ክብር_ለሰማዕታት
#Ethiopia



9/9
ፎቶዎቹ ከተለያዩ ድረገፆች
ሙሉውን ታሪክ ለማግኘት
https://www.sewasew.com/phrases/5548?withDetails=
#ክብር_ለሰማዕታት
#Ethiopia



9/9