ምን ያህሎቻችን የአስራ ሦስቱን ወራት ስያሜ እናውቃለን?

መልካም ንባብ🖤📖 1/14
<<መስከረም>>🗓
መስከረም ማለት ክረምቱ አለፈ ማለት ነው።
መስ - ማለት አለፈ ሲሆን
ከረመ - ማለት ደግሞ ክረምት ነው።

መነሻ ቃል ፦ መስ እና ከረመ 2/14
<<ጥቅምት>> 🗓
ጥቅምት ማለት ጠቃሚ ጊዜ (ስራ የሚሰራበት ጊዜ) ማለት ነው።

መነሻ ቃል ፦ ጠቀመ 3/14
<<ኅዳር>> 🗓
ሕዳር ማለት ማደር ማለት ነው።
ገበሬው ለአስመራ ጊዜ ማሳ ውስጥ ለጥበቃ ማደሩን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ ኀደረ 4/14
<<ታኅሳስ>>🗓
ታሕሳስ ማለት መመርመር ማለት ነው።
ገበሬው በመኸር ወቅት ሰብል መመርመሩን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ ኀሠሠ 5/14
<<ጥር>>🗓
ጥር ማለት ጠረረ፣ነጻ (ብልጭ አለ) ማለት ነው።
የፀሐይን ግለት ወቅት ያሳያል።

መነሻ ቃል ፦ ነጠረ 6/14
<<የካቲት>>🗓
የካቲት ማለት መክተቻ ማለት ነው።
የእህል መክተቻ ወቅት መሆኑን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ ከቲት 7/14
<<መጋቢት>>
መጋቢት ማለት መመገብ ማለት ነው።
ገበሬው በጎተራው የከተተውን የሚመገብበት ወቅት መሆኑን
ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ መገበ 8/14
<<ሚያዝያ>>🗓
ሚያዝያ ማለት ጎለመሰ፣ ጎበዘ (ሚስት ፈለገ) ማለት ነው።
የሰርግ ወር መሆኑን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ መሐዘ 9/14
<<ግንቦት>>
ግንቦት ማለት ገነባ ፣ ሠራ ፣ ቆፈረ ፣ ሰረሰረ ማለት ነው።
ገበሬው ለእርሻ መሬቱ መዘጋጀቱን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ ገነበ 10/14
<<ሰኔ>>🗓
ሰኔ ማለት የሚያምር ነገር ማለት ነው።
ገበሬው ዘርቶ መሬቱ ማማሩን ያመለክታል።

መነሻ ቃል ፦ ሰነየ 11/14
<<ሐምሌ>>🗓
ሐምሌ ማለት መልቀም ማለት ነው።
ገበሬው መልቀሙን ያመለክታል። (በተለይ ለጎመን)

መነሻ ቃል ፦ ሐመለ 12/14
<<ነሐሴ>>🗓
ነሐሴ ማለት ማቅለል (መተው) ማለት ነው።
የክረምቱን መቅለል ያሳያል።

መነሻ ቃል ፦ አናሕስየ 13/14
<<ጳጉሜ>>🗓
ጳጉሜ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው።
ተጨማሪ ወር መኖሩን ያመለክታል።(የግሪክ ቃል ነው)

መነሻ ቃል ፦ ኤጳጉሚኖስ 14/14
Retweet It🖤
You can follow @Mikiyas_Beyene.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.