1/9- የሀገራችን ችግር ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይት ያስፈልጋል:: በጦርነት የሚፈታ አንዳችም ችግር የለም:: በጦርነት ተሸናፊ እንጂ አቸናፊ የለም::
2/9-
የ80 ብሄርና ብሔረሰቦች ሀገር እንጂ የ3 ብሄር ሀገር አይደለችም:: ሁሉም ብሄሮችና "ብሄር አልባዎች" በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ እኩል መብት አላቸው::

3/9- በትግራይ ክልል እየደረሰ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ መቃወም ማለት ህወሃትን መደገፍ ማለት አይደለም:: የሰብአዊ እርዳታን ለፖለቲካዊ ግብ መጠቀም አውሬነት ነው::
4/9- ሱዳን የኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛትን ወራለች:: የውጪ ወረራ ሲመጣ በጋራ ጠላትን መመከት የዜግነት ግዴታ ነው:: መንግስት በዚህን ጊዜ ብሄራዊ መግባባት በሚያመጡ ነገሮች ላይ የመስራት ግዴታ አለበት::
5/9- ሻዕቢያ የኢትዮጵያ ወዳጅ ሀገር ከሆነ የኮ/ል በዛብህን በህይወት መኖርና አለመኖር ለቤተሰቦቹ ያሳውቅ!! በህይወት ከሌሉ አስክሬናቸውን በክብር ይመልስ!
6/9- አንድም የኤርትራ ወታደር በሀገራችን ውስጥ በድብቅ መንቀሳቀስ የለበትም:: ትግራይ ህዝብ ዘረፋና ወንጀል እየፈፀሙ ያሉት በአስቸኳይ መውጣት ይገባቸዋል::
7/9- በመተከል ዞን በአማራ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት መቆም አለበት:: ሰው በማንነቱ ብቻ የሚያስጠቁ የፖለቲካ ቁማርተኞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው::
8/9- ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በመንግስት የፀጥታ አካላት የሚደርሰው ጥቃት ግድያና ሰቆቃ በአስቸኳይ መቆም አለበት::
9/9 ለህይወትዎ ዋጋ ይስጡ! ማስክ ያድርጉ! ማስክ በማድረግ ለሌላው ወዳጅ ዘመድዎ ጥንቃቄ ያድርጉ!
ፅሁፉ የሰዋሰው ግድፈት ካለው ይቅርታ!
ፅሁፉ የሰዋሰው ግድፈት ካለው ይቅርታ!
