አክስቴ የሁመራ ከተማ ነዋሪ ናት:: ሰሞኑንየመገናኛ መንገዶች ሁላ በመቋረጣቸው ቤተሰብ ሲጨነቅ ነበር የሰነበተው ከአራት ቀናት በፊት ግን አክስቴ በሱዳን ስልክ ደውላ ወደ ሱዳን የድንበር ከተማ መሰደዳቸውን ነገረችን:: ጭንቀታችን ባሰ /1
እሷ ካልደወለች እኛ መደወል ስለማንችል ሁላችንም ስልካችን ላይ እንዳፈጠጥን በሁለተኛው ቀን ደወለች:: ከ19 አመት ወንድ ልጇ ጋር ተጠፋፍተው እንደነበር: ወደ ሱዳን የሄዱበት ምክንያትም ቀበሌዎች(ትህነግ) በየሰፍሩ እየዞሩ /2
የአብይ መንግስት በአውሮፕላን ሊጨፈጭፋችሁ ነው ስላሏቸው እንደሆነና ህፃናትና ወጣቶችን እያፈሱ በመኪና ይጭኗቸው እንደነበር ነግራናለች:: ልጇም ከአፈሳ አምልጦ ተደብቆ እንዳለና ደህና መሆኑን መስማቷን አሳወቅችን:: /3
በማግስቱ መከላከያ ከተማዋን መቆጣጠሩንና አካባቢውም ሰላም እንደሆነ በመስማታቸው ለመመለስ እየተዘጋጁ እንደሆነ ነገረችን::
ትናንት አክስቴ ሁመራ ገብታለች:: ከልጇ ጋር በአካል ባትገናኝም/ 4
እዚያው ከተማ ውስጥ ተደብቆ እንዳለና አሁን ሄዳ ልታመጣው እንደሆነ ነግራናለች:ትህነግ አለም አቀፉ ማህበረሰብ መንግስት ላይ ግፊት እንዲያደርግ ለማስገደድ ህዝቡን እንዲሰደድ እያስገደደች መሆኑን መረዳት ችያለሁ #Ethiopa
You can follow @SoloEthioZ.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.