👑 ንግሥት ካሲዮፕያ ታላቋን ሀገር ኢትዮጵያን ከክርስቶስ ልደት በፊት 1890-1871 ለ19 ዓመት መራች። ይህች አስተዋይ ኢትዮጵያዊት ንግሥት ከባለቤቷ ከንጉሥ ሴፌውስ እና ከቆንጆዋ ልጇ ከልዕልት አንድሮሜዳ ጋር በመሆን ጠፈርን የመመርመር በሥነ ፍጥረትም
የመደነቅ ሰፊ ብቃት ነበራት። እነዚህ ኢትዮጵያውያኑ የንጉሣውያን ቤተሰቦች ስማቸው ምድር ላይ ተተክሎ መቅረት እንደሌለበት ያስቡ ነበር፡፡ በሥነ ፍጥረት በእጅጉ በመማረክ ይልቁኑ በምሽቱ ሰማይ ላይ የተለያየ ቅርጽ እየሠሩ የዕንቁ ፈርጥ መስለው -
በሰማይ ላይ እያበሩ እያብረቀረቁ የሚታዮትን ከዋክብት በጥንቃቄ ያስተውሉ ነበር፡፡ ይህ ዝናቸው እስከ ግሪክ ተሰምቶላቸው ስለነበር ግሪካውያኑ በኢትዮጵያውያኑ ንጉሣውያን ቤተሰቦች በመደነቅ ብዙ ማይቶሎጂዎችን ስለእነርሱ ይናገሩ ነበር፡፡
ከነዚያ ከሚመለከቷቸው ሕብረተ ከዋክብት ውስጥም ሦስቱን ንጉሥ ሴፌውስ፣ ንግሥት ካሲዮፒያና ልዕልት አንድሮሜዳ በስማቸው እንዲሰየምላቸው አድርገዋል፡፡ ይህ ታሪክ የሚታወቀው በእኛ ብቻ ሳይሆን በስነ ከዋክብት ጥናት ታላቅ ደረጃ ላይ በደረሱት -
በጥንታውያን ግሪኮችና ዛሬም ባለው የሥነ ከዋክብት የሳይንስ ጥናት ጭምር ነው፡፡
በ2ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ግሪካዊው የሥነ ከዋክብት ተመራማሪ ፕቶሎሚ ከመዘገባቸው 48 ሕብረተ ከዋክብት ውስጥ ሦሥቱ በኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ካሲዮፒያ፣
በኢትዮጵያዊው ንጉሥ ሴፌውስና በኢትዮጵያዊቷ ልዕልት አንድሮሜዳ ስም ነበር፡፡
ይህ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሕብረተ ከዋክብትን በመሰየም ያደረገችው ታላቅና ገናና ሥራ የማይካድ እውነት ነውና እጅግ በበርካቶች ተመራማሪዎችና ምርጥ ሳይንቲስቶች
የተዋቀረው የዓለም ዐቀፉ አስትሮኖሚ ኅብረት ለዚህ ድንቅ ታሪካችን ዕውቅናን በከፍተኛ ደረጃ በመስጠት ከመዘገባቸው 88 ሕብረተ ከዋክብትን ሦስቱ በንግሥት ካሲዮፒያ፣ በንጉሥ ሴፌውስና በልዕልት አንድሮሜዳ ስም ነው፡፡
ምንጭ- አንድሮሜዳ(መፅሐፍ) በዶ/ር ሮዳስ ታደሰ አና ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ
ልዕልት አንድሮሜዳ ( Image: by Toradh (Deviant Art))
ካሲዮፕያ የኢትዮጵያ ንግስት
(Image: http://vectorstock.com  and http://utahsadventurefamily.com )
ሴፌውስ የኢትዮጵያ ንጉስ
(Image: meteo vaggio and http://vectorstock.com 
አንድሮሜዳ የኢትዮጵያ ልዕልት ( Image: http://pathtospace.com  and http://universavvy.com )
You can follow @Oliad_D.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.