Thread 1
ከንጉሥ ነፍጥ አንጋች እስከ መከላከያ ስራዊት።
የኢትዮጵያ ወጥቶ አደር (ወታደር)
በኢትዮጵያ የዘመናዊ ጦር አደረጃጅት ጥንስስ የተጀመረው ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ ወደ ስልጣን ከመጡ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1855 በሁዋላ ነበር
Thread 2
ዓፄ ቴዎድሮስን መደበኛ ጦር እንዲያቋቁሙ ያማከራቸው ትውልዱ አየርላንዳዊ የሆነና በምጽዋ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የመጣ ጆን ቤል የሚባል ሰው ነው። በሁዋላ እንደውም ስሙን 'ዮሐንስ' ብለው አስጠምቀው የሊቀመኳስነት ማዕረግ ሰጥተው..
Thread 3
ኢትዮጵያዊት ድረው ባለሟላቸው አድርገውት ከሳቸው ጎን ከጠላቶቻቸው ጋር ሲዋጋ የሞተ ወዳጃቸው ነው። ታዲያ ጆን ቤል (ሊቀመኳስ ዮሐንስ) በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመቻዎች ወቅት ነፍጥ አንጋቾቻቸው ገባሮች እየዘረፉ ራሳቸውን ሲቀልቡ ተመልክቶ..
Thread 4
ባገሩ ወታደር ደሀውን ሳያስቸግር በመንግስት ድርጎ (ደሞዝ) እየተሰጠው እንደሚተዳደር ፣ በጦርነት የሞተ እንደሆነም ቤተሰቦቹ እንዳይቸገሩ ድርጎው ለነሱ እንደሚተላለፍና ሌሎችንም የውትድርና ደንቦች አስረዳቸው።
ንጉሱ ሀሳቡን ስለወደዱት..
Thread 5
ይህ እንዲሆን ፈቀዱ። ይሁንና ለድርጎ ይከፍሉት የነበረው የማርያ ቴሬዛ ቶላር (MTT) በመወደዱ በምትኩ ለነፍጥ አንጋቾቻቸው ርስት (መሬት) በመስጠት አደረጃጀቱን ሞከሩት። ይህንንም እንዲያስፈጽሙ የጦር አለቃቸውን ወልቃይቴውን..
Thread 6
ፊታውራሪ ገብረህይወትን (ገብርዬ) ሾሙ። ሆኖም ይሄ ለአንጋች መሬት ማከፋፈል በተለይ በጊዜው ትግሬን (ትግራይን) ያስተዳድሩ ከነበሩት ደጃዝማች ውቤ ጋር ግጭት በመፍጠሩ እምብዛም ሳይሳካ እንደቀረ ተክለጻድቅ መኩርያ በጻፉት...
Thread 7
" ዐፄ ቴዎድሮስና የኢትዮጵያ አንድነት" በተሰኘው መጽሐፍ ጽፈውታል። አቤ ጉበኛ ስለ ዐፄ ቴዎድሮስ በጻፈው "አንድ ለናቱ" መጽሐፉ ደግሞ መኳንንቶቻቸው አንጋቾቹ ከነሱ የሚተካከከል እጀ ጠባብ መልበሳቸውን በእጅጉ እንደተቃወሙ ይተርካል።
Thread 8
በዚህ ሁኔታ ዘመናዊ የጦር ሰራዊት የመመስረት ህልማቸው የተጨናገፈው ዐፄ ቴዎድሮስ ሙከራቸው ባይሳካም እስከ ህልፈታቸው አቅራቢያ ጋፋት ላይ መድፍ እስካሰሩበት ጊዜ ድረስ በዚሁ ስራ ለተጠመዱት ሰዎች ሁሉ ድርጎ በመስጠት ገፍተውበት ነበር።
Thread 9
ውትድርና በዮሐንስ ፬ኛ ዘመን
ዐፄ ቴዎድሮስን ለአጭር ጊዜ የተኩት አገዌው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ በአማቻቸው ደጃዝማች ካሣ ምርጫ (ዐፄ ዮሐንስ) በጦርነት ከተሸነፉ በሁዋላ አዲሱ ንጉሥ ዐፄ ዮሐንስ የኃይል ሚዛንን የማስተካከል እውቀት ነበራቸው።
Thread 10
ተክለጻድቅ መኩርያ በጻፉት "ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት" በሚለው መጽሐፋቸው ከንግስናቸው በፊት ደጃዝማች ካሳ ምርጫ በመባል የሚታወቁት ዐፄ ዮሐንስ የዐጼ ቴዎድሮስ አንጋች የነበረ በርካታ ሰራዊትና ከእንግሊዞች ደሞ ብዙ መሳርያ..
Thread 11
አግኝተው ስለነበር የሚስታቸውን ወንድም ዐፄ ተክለጊዮርጊስን መገዳደር ከባድ አልሆነባቸውም። ካሣ ምርጫን (ዐፄ ዮሐንስን) ለማስፈራራት ዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ "ሰራዊቴ እንዲህ የበዛ ነው" ብለው ኩንታል ጤፍ ቢልኩባቸው ካሣ ምርጫ (ዐፄ ዮሐንስ)
Thread 12
ጤፉን ቆልተው መልሰው ወደ ዐፄ ተክለጊዮርጊስ በመላክ "ሰራዊትህ ቢበዛ እንደዚህ እቆላዋለሁ" ብለዋቸዋል ብለው ተክለጻድቅ መኩርያ በዚሁ "ዐፄ ዮሐንስና የኢትዮጵያ አንድነት" በተሰኘው መጽሐፍ ጽፈዋል። ይህ ማለት እንግዲህ ዐጼ ዮሐንስ..
Thread 13
ከዐፄ ቴዎድሮስ ወደሳቸው የሄደ የተደራጀ ወታደር እንደነበራቸው አመላካች ነው።
እንዳሉትም የባለቤታቸው ወንድም የሆኑትን ዐፄ ተክለጊዮርጊስን በቀላሉ አሸንፈው ንግስናውን ወደ እሳቸው አዞሩት። ከጥቂት አመታት እስር በሁዋላ
Thread 14
ህይወታቸው ስላለፈው አማቻቸው ዐፄ ተክለጊዮርጊስ እህት የዐፄ ዮሐንስ ባለቤትም እንዲህ ተገጠመ።
የገደለው ባልሽ፣
የሞተው ወንድምሽ፣
ሀዘንሽ ቅጥ አጣ፣
ከቤትሽም አልወጣ።
Thread 15
ዐፄ ዮሐንስ ከሳቸው ቀደም ሲል ከነበሩ ነገስታት ለየት ያለ የአስተዳደር ዘዴ ነበራቸው። የሀይል ሚዛንን ጠንቅቀው በመመዘን ስልታዊነትና ብልሀት ነበራቸው። ከዐፄ ቴዎድሮስ በፊት የነበረው የዘመነ መሳፍንት መቆራቆስ ተመልሶ እንዳይመጣ..
Thread 16
በየአካባቢው የነበሩ ልዑላንን ግዛቶቻቸውን በማካለል ሙሉ "የንጉሥነት" ስልጣን ሰጡ። በዚሁ መሰረት፣ የሳቸውን "ንጉሠ ነገስትነት" የተቀበሉትን ምኒሊክን "ንጉሠ ሸዋ" ተክለሐይማኖትን ደግሞ "የጎጃም ንጉሥ" አድርገው ሾሙ።
Thread 17
ከነዚህ ነገስታት ግብር ከመሰብሰብ ሌላ አንጋችና (ወታደር) መሳርያም እንዲያዋጡ ይጠይቁ ነበር። በነዚሁ የአካባቢ 'ነገሥታት' መካከልም ግጭት ሲፈጠር እሸማገሉ የሀይል ሚዛኑን ይጠብቁ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሰራዊታቸው ከቀድሞ ነገስታት ይልቅ
Thread 18
የተሻለ ስብጥር የነበረው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ዐፄ ዮሐንስ የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ የሆነ ሰራዊታቸውና እየተስፋፋ በመጣው ግዛታቸው የሚኖረው ህዝብ አንድ መግባቢያ ቋንቋ እንዲኖረው በማሰብ ምንም እንኳ እሳቸውና መኳንንቶቻቸው ..
Thread 19
የትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ቢሆኑም አማርኛ ቋንቋ የመንግስታቸው ቋንቋ እንደሆነ አውጁ። በሰራዊታቸውና በህዝባቸው መካከል መክፋፈል እንዳይኖር ኢትዮጵያዊ ስሜትን አጥብቀው የሚሰብኩ አልፎ አልፎም ለዚህ ዘመን ተቀባይነት የሌለው ቅጣትን
Thread 20
የሚጥሉ እንደነበሩ ከታሪክ መዛግብት ያጣቀሱት የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ታቦ ምቤኪ በአንድ ወቅት ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሑፍ በዝርዝር አስረድተዋል።
Thread 21
ይሁንና በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የዐፄ ዮሐንስ ጭካኔ የተሞላበት ቅጣት ሰለባ እንደነበሩ ሳይነገር የሚታለፍ አይደለም። ሆኖም ዐፄ ዮሐንስ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሰራዊት ጥንስስ አካል መሆናቸው የማይካድ ነው።
Thread 22
ውትድርና በዳግማዊ ምኒሊክ
ዮሐንስ ፬ኛን የተኩት ዳግማዊ ምኒሊክ እንደ ዐፄ ቴዎድሮስና ዐፄ ዮሐንስ ሁሉ ዘመናዊ ሰራዊት የማደራጀት እቅዱን ቀጠሉበት። በተለይ የዛሬውን የደቡብ ፣ ደቡብ ምዕራብና ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያን ወደ ማእከላዊ
Thread 23
መንግስት ባጠቃለሉበት ጊዜ በነፍጥ አንጋችነት የተጠቀሙት በብዛት የዚያኑ የአካባቢውን ሰው ነበር። እስከ አድዋ ዘመቻ በዚሁ ሁኔታ ያሰባሰቡት ሰራዊት ነበር ለዓድዋ ዘመቻ በቀላሉ ሰራዊት እንዲያሰባስቡ የረዳቸው።
Thread 24
በዓድዋ ድል የነሳው ቁጥሩ 100ሺ ያህል የሚገመተው ሰራዊቱ ከድል እንደተመለሰ ከውስጡ ብርቱው ተመርጦ በድርጎ (ደሞዝ) እየተዳደረ ቋሚ ሰራዊት እንዲሆን በንጉሡ ተወሰነ። ይሁንና በድርጎ ድልድል ሰራዊቱን ያዙ የነበሩ መኳንንቶች ጭቅጭቅ አመጡ
Thread 25
በተለይ የፈረሰኞች አለቃ የነበሩት ደጃዝማች ጎበና ዳጬና ብዛት ያለው ሰራዊት የነበራቸው ደጃዝማች ባልቻ ሳፎ (አባ ነፍሶ) ለአንጋቾቻቸው በተመደበው ድርጎ "እኔ ይበልጥ እኔ ይበልጥ" ቅራኔ ስለገቡ የሁሉ አለቃ ራስ አሉላ ሰራዊት በድርጎ..
Thread 26
ስራዊት ማደራጀቱ እንዲቆይ ንጉሡን አማከሩ። ይሁንና ቁጥሩ ቀላል የማይባል ነፍጥ አንጋች ድርጎ እየተሰጠው በእንጦጦ እንዲሰፍር ተደረገ። ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ  አዛዡ እንዲሆኑ ሆኖ የመጀመርያው ድርጎኛ ወታደር ተፈጠረ።
Thread 27
ዳግማዊ ምኒሊክ ካለፉ በሁዋላ ልጅ ኢያሱ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቅድሚያ ከሰጡት ነገር አንዱ በተደራጀ ነፍጥ ተሸካሚ የአዲስ አበባ ከተማን ማስጠበቅ ነበር። እናም ወጣቶችን መልምለው "የአራዳ ዘበኛ" በሚል የመጀመርውን ፖሊስ ሰራዊት መሰረቱ።
Thread 28
የስልጣን ዘመናቸው በሶስት አመት ብቻ የተቀጨው ልጅ ኢያሱ ከስልጣን ሲወገዱ አባታቸው ራስ ሚካኤል (ቅድመ ክርስትና ስም መሐመድ) የልጃቸውን ከስልጣን መውረድ ተቃውመው ከራስ ተፈሪ መኮንን (በሁዋላ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ)
Thread 29 
ባደረጉት ጦርነት (የሰገሌው ጦርነት በመባል የሚታወቀው) አብዛኛው በራስ ተፈሪ መኮንን በኩል የተሰለፈው ተዋጊ አዲስ አበባን ለመጠበቅ የተዘጋጀ አዲስ ምልምል ነበር። ብዙ ሰው ባለቀበት በሰገሌው ጦርነት ራስ ሚካኤል ከተሸነፉ በሁዋላ፣
Thread 30
..ሌላ ተቀናቃኝ ተነስቶ በቅላሉ ሰራዊት መልምሎ ሊያጠቃቸው እንደሚችል በመገንዘባቸው ፈጥነው የተደራጀና በወጉ የታጠቀ ሰራዊት ማደራጀት እንደሚያስፈልጋቸው ተገነዘቡ። ለዚሁም ተግባር በጊዜው የቤተመንግስቱን ጥበቃ ሀላፊነት
Thread 31

የተስጣቸውን ደጃዝማች ከበደ ተሰማን (የአምባሳደር ካሣ ከበደን አባት) አሰማሩ። ይህን ተከትሎም ልክ እንደ አራዳ ዘበኛ (ፖሊስ) ድርጎ የሚቆረጥለት ሳርያን የለበሰ መለዮ የሚያጠልቅ ስሙ "የክብር ዘበኛ" የተባለ ሰራዊት ተደራጀ።
Thread 32
የመጀመርያዎቹ ክቡር ዘበኞች የሰለጠኑት በእንግሊዝ ቅኝ በነበረችው  ኬንያ ሄደው የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያንና እንግሊዞች ነበሩ። አረማመዳቸውና አለባበስቸው ያማረ ወታደሮች ባለግርማ ሞገሶች እንደነበሩ ባህሩ ዘውዴ በመጽሐፋቸው ተርከዋል
Thread 33
ኢጣልያ በ1935 ኢትዮጵያን ስትወር የኢትዮጵያ ቋሚ ሰራዊት ይሄው የክብር ዘበኛ ጦር ብቻ ነበር። ብዙ የክብር ዘበኛ አባላት ሀገራቸውን በድንገት ከወረራት ወራሪ ኃይል ሲከላከሉ ከፍተኛ መስዋእትነት ከፍለዋል። 
የፋሽስት ኢጣልያ ጦር
Thread 34
ከኢትዮጵያ ከተባረረ በሁዋላ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ኢትዮጵያን የማዘመኑን ስራ የጀመሩት ወጥ የሆነ አስተዳደር ያለው የጦር ሀይል በማቋቋም ነበር። ለዚህ በምሳሌነትም ቀድሞውን ክቡር ዘበኛ እንደገና በማቋቋም ሌሎችንም ክፍሎች
Thread 35

ማደራጀት ነበር። በ2ኛው የዓለም ጦርነት ማግስት  በ1950 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሜሪካ አስተባባሪነት በኮምዮኒስት ቻይና የምትደገፈው ሰሜን ኮርያ ባካባቢው ተጽእኖዋን ለመግታት በሚል ባድረገው ጥሪ
Thread 36
ኢትዮጵያ የነበራትን ብቸኛ ዘመናዊ ጦር 'ክቡር ዘበኛ'ን እንደምታሰልፍ ቃል ገባች።ዐፄ ኃይለስላሴ ይህንን ያደረገቡት ምክንያት ዓለምዐቀፍ እውቅናን ለሀገራቸውና ለመንግስታቸው ለማስገኘት ነበር።
Thread 37
በጊዜው ነጻ የአፍሪካ ሀገር መኖርን ብዙዎች አያውቁም ነበር። ኢትዮጵያ ወደ ኮርያ ሰራዊቷን በመላክ የጥቁር ህዝቦችን ሉዐላዊነትና ክብር ለዓለም አሳይታለች።
Thread 38
በዚህ ሁኔታ ነበር የኢትዮጵያ ሰራዊት ከክቡር ዘበኛ አንስቶ ወደ እግረኛ ጦር ስራዊት ፣ ታንከኛ፣ መድፈኛ ፣አየር ኃይል ፣ባህር ኃይል ፣ ወታደራዊ ፖሊስ በአራቱም ማዕዘናት ባሉት እዞች ተከፋፍሎ የተቋቋመው ።
Thread 39
ሁሉም በሚባል ደረጃ የክፍሉ አዛዦች አውሮፓና አሜሪካ አሉ በሚባሉ የውትድርና ማሰልጠኛ ሰልጠናዋል። እነ ጄኔራል ዓብይ አበበ፣ ነጋ ኃይለስላሴ፣ መንግስቱ ንዋይ፣ኃይሌ ባከዳኝ፣አማን ሚካኤል አንዶም ታላላቅ ወታደራዊ ምሑራን ነበሩ።
Thread 40
በ1960 እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የክቡር ዘበኛ አዛዥ ብርጋዴር ጄነራል መንግስቱ ንዋይ ለውጥ ያስፈልጋል በሚል ንጉሡ ወደ ብራዚል በሄዱበት በሞከሩት  የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በሙከራው አድራጊዎች በክቡር ዘብኛና በሙከራው አክሻፊዎች
Thread 41
በጦር ሰራዊት መካከል ቅራኔና ልዮነት ተፈጠረ። ለንጉሡ ፍጹም ታማኝ እንዲሆን የሚጠበቀው ክቡር ዘበኛ ንጉሡን ለማስወገድ ሲጥር ዳር አገር ጠባቂው ጦር ሰራዊት የንጉሡን ስልጣን መታደጉ ብዙዎችን አስደመመ።
Thread 42
ይህንን የታዘቡት ዐፄ ኃይለስላሴም ከዚያን ጊዜ በሁዋላ ፣ ለክቡር ዘበኛ አዛዥ የሚመርጡት ከጦር ስራዊት ነበር። በዚያን ጊዜ ንጉሡን ከድተዋል ተብለው የተጠረጠሩት የክብር ዘበኛ ዝቅተኛ አባላት በአነስተኛ አመታት እስር እንዲቀጡ ሲደረግ
Thread 43
ጥቂቶቹ ምህረት ተደርጎላቸው ተመልሰዋል። በወቅቱ ለጥቂት ጊዜያት ከታሰሩት የክብር ዘበኛ አባላት መካከል አንዱ ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ነበር
Thread 44
በ1966 እንደ ኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር በደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ሰበብ ከካምፑ ወጥቶ፣ 'ጥያቄዬ እስኪመለስ' በሚል ሰበብ አዛዦችን በበታች መኮንኖች ካሰረ በሁዋላ ንጉሡን ከስልጣን ያሰወገደው ሰራዊት ከስህተት የጸዳ ሕፀፅ የሌለበት አልነበረም።
Thread 45
በወታደራዊው የደርግ ዘመን አመራሩ ፍጹም አምባገናዊ ስርዐት በማስፈን ብዙዎች ህይወትና ንብረታቸውን አጥተዋል። "ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር" በሚል ግትር መፈክር ሀብት ደቆ የእርስ በርስ ጦርነቱ በድርድር እንዳይፈታ መንገድ ተዘግቷል።
Thread 46
ይባስ ብሎ ደግሞ ሀገሪቱ በከፍተኛ በምርጥ ሁኔታ ያሰለጠነቻቸው ብዙ ልምድና እውቀት የነበራቸው 12 ጄኔራል መኮንኖችን መንፈቅለ መንግስት ሞክራዋል በሚል ረሽኖ የሰራዊቱን ሞራል ማላሸቁ ነው። ይህ ለሰራዊቱ ሽንፈት በር ከፋች ክስተት ነበር
Thread 47
ይሁን እንጂ የሀገሪቱን ሉዐላዊነት ለመጠበቅ ሁልጊዜ ዝግጁ የሆነ ጦር ነበር። ግራ ዘመም መርዘኞች (ኢህአፓ መኢሶን እና ሌሎችም) ውስጡ ሰርገው ገብተው ሲከፋፍሉት እንኳን ፣ ኢትዮጵያ ስትወረር እንዳንድ ተነስቶ ሀገሩን ድንበሩን አስከብሯል
Thread 48
በእርስ በርስ ጦርነቱ አማጽያን ሲያሸንፉ ደግሞ ፣ ይህ ሰራዊት ምን አይነት ስነስርዐት ያለው ህዝባዊ መሆኑን ያሳየበት ነበር። ድል ከተነሳበት የጦር ሜዳ ሲመለስ፣ በእጁ ክላሽ፣ በወገቡ ቦምብ ታጥቆ ነበር።
Thread 49
ረሀብ እየራበው ረጅም መንገድ ወደ ቤተሰቦቹ ለመመለስ እየተጓዘ፣ ወሀ ከሰጡት አመስግኖ ይጠጣል እንጂ፣ የያዘውን መሳርያ ተጠቅሞ
ማንንም አልዘረፈም፣ "
Thread 50
"ማን አለብኝ" ብሎ ንብረት አላወደመም "በጄ መሳርያ አለ አጥፍቼ እጠፋለሁ" ብሎ አዲሶቹን መሪዎች አልተገዳደረም በስርዐት ወደቤተሰቦቹ ተመለሰ እንጂ። ከኢህአዴግ ትልቁ ጥፋት ዛሬም መዘዙ የማይለቀው ይህንን ሰራዊት ያለአገባብ መበተኑ ነው።
Thread 51
ሆኖም ጥቂት አመታት ቆይቶ አሁንም "የኢትዮጵያ ድንበር ተደፍሯልና ትፈለጋለህ" ሲባል ተበደልኩ ብሎ ቂም ሳይዝ እንደገና ሊዘምት እንደገና ሊሰዋ ወደ ሰሜን ተመመ።
Thread 52
ለፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባርያ ሳይሆን ታማኝነቱ ለሀገሩ ብቻ ስለሆነ...
"..ልሙት ልሰዋ ደስ ብሎኝ ስቄ
ለሀገሬ ክብር እኔ ወድቄ.." ብሎ ነው ባድመ የዘመተው።
Thread 53
ዛሬ ባለው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ባለስልጣናቱ ምክትል ኤታ ማዦር ሹሙን ጄኔራል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ የዚህ የቀድሞ ሰራዊት አባል የነበሩ ናቸው።
Thread 54
በደርግ ዘመን በነበረ የጥቂት አመራሮች ብልሹ አመራር ይህ ሀገር ወዳድ ባለውለታ ፍጹም ስርአት የተላበሰ ሰራዊት መውቀስ የለበትም። ይህንን እንድጽፍ ያነሳሳኝ በአንዳንድ ሀገርን መከላከል ምን እንደሆነ ባልተረዱ ድኩማን ይህ ሰራዊት
Thread 55
ሲብጠለጠል ታዝቤ ነው። መስዋእትነትን መክፈል ማለት ምን እንደሆነ ቅንጣት ታህል የመገመት አቅም ሳይኖራቸው እነዚህ ጀግኖችን የቀድሞውን ወይም ያሁኑን ወታደር የማሽሟጠጥ የማንጓጠጥ የሞራልም የአስተሳሰብም የስነምግባርም ብቃት የላቸውም
@threadreaderapp Please unroll
You can follow @RegulaeMea.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.