Thread

የፈረቃ ለቅሶ

የሀጫሉን ግድያ ተከትሎ በኦሮሚያ ንጹሀን ዜጎች ላይ ብሄር እና ሀይማኖት ተኮር ጭፍጨፋ ሲፈጸም ብዙዎች የተቃውሞ ድምጻችንን አሰምተናል - ትክክል ነበር። 1/16
"የኦሮሞ ልሂቃን ለምን ድርጊቱን አያወግዙም?" የሚሉ በርካታ ድምጾችም ነበሩ - ትክክል ነበር። ብዙዎች በምሬት አልቅሰዋል። በሚያሳዝን ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያ ተጽኖ ፈጣሪ ከሚባሉ ኦሮሞ ልሂቃን ድርጊቶቹን ያወገዙ ጥቂቶች ነበሩ።
አንዳንዶች ጭራሽ የሚወጡትን መረጃዎች ተክክለኛነት እስከመጠራጠር ደርሰው ነበር፤ ይህ መቼም ለተጠቂዎች ዳግም ሞት ነበር።
ባለፉት ጥቂት ቀናት ደግሞ ኦሮሚያ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የተቃውሞ ሰልፍ በወጡ ዜጎች ላይ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በወሰዱት እርምጃ ብርካቶች መገደላቸውን የአሜሪካ ድምጽ ዘገባ፣ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን መግለጫ፣
እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ቃል አቀባይ ለኢሳት በሰጡት ቃለ ምልልስ ጭምር አረጋግጠውልናል። ይህንን የመንግስት ተመጣጣኝ ያልሆነ የሀይል እርምጃ ተከትሎ በተገደሉ ዜጎች ምክንያት ተቃውሞውን እያሰማ እና ለቅሶ የተቀመጠው
በአመዛኙ የኦሮሞ ማህበረሰብ መሆኑን እየተገነዘብን ነው።

ኦሮሚያ ላይ እብሪተኞች የገዛ ወገናቸው ላይ ሲዘምቱ ገሚሶች፣ አሁን ደግሞ መንግስት ዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈጽም የተቀረው ገሚስ ከማዘን አልፈን፣ አብረን ማውገዝ እና ማልቀስ ለምን ተሳነን?
ብዙዎች በዚህ ግራ ሲጋቡ፤ ሲያዝኑ፤ ሲበሳጩ ተመልክቻለሁ። ነገር ግን ያልዘራነውን ከየት አምጥተን ልናጭድ ነው? በሰላሙ ጊዜ አንድነትን፣ መተባበርን፣ መተሳሰብን ስንሰብክ ነው የቆየነው
ወይንስ ሁላችንም በየጎጇችን "እኛ እና እነሱ" ስንባባል ነው የከረምነው? "ኦሮሞ ይህንን አያደርግም" ብለው በድፍረት ሲናገሩ ነበር አንዳንዶች ያ ሁሉ ዜጋ በግፍ ሲገደል እና ሻሸመኔ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ ስትወድም።
በዚህኛው ዙር ደሞ "መንግስት ቀደማቸው" በማለት በመንግስት ታጣቂዎች ህይወታቸው ባለፈ ዜጎች ላይ የተሳለቁ ወገኖችም አያየን ነው።

ሞት ሞት ነው። ገዳይ ገጀራም ይያዝ፣ ክላሽ ያው ገዳይ ነው።
ገዳይ የሰፈር ጎረምሳም ይሁን፣ መለዮ ለባሽ ያው ገዳይ ነው። ሟች ኦሮሞም ይሁን አማራ፣ ወላይታም ይሁን አፋር፣ ሟች ያው ሟች ነው። እነዚህ ሟቾች ሁሉ የኢትዮጵያን አፈር ነው የሚለብሱት፤
ነገር ግን በህይወት ያለነው በፈረቃ እንጂ በጋራ ማልቀስ አልቻልንላቸውም። ደግሜ እላለሁ ያልተዘራ አይታጨድም። ግፍ ሲፈጸም አብረን ለማውገዝ፣
አብረን ለማልቀስ በደህናው ጊዜ የሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ ሳይሆን የሚያስተሳስረን ጉዳዮች ላይ ማተኮሩ ነው የሚሻለን። ሰሞኑን የተቃውሞ ሰልፎቹን ሲጠሩ ለነበሩ ሰዎች ጥሩ አመለካከት ላይኖረን ይችላል፤
ነገር ግን ሰልፍ ለወጡ ወጣቶች የመንግስት ምላሽ ጥይት ሊሆን በምንም መስፈር አይገባም። ከዚህ የተሻለ ምላሽ ከመንግስት መጠበቅ ግድ ይለናል።
በኦሮሚያ ያ ሁሉ ግፍ ሲፈጸም መንግስት ንጹሀን ዜጎችን ለምን አልጠበቀም ብለን ተገቢ ጥያቄ ያነሳነውን ያህል፣ ተቃውሞ የወጡ ዜጎችንስ ለምን አልጠበቀም በማለት ሀላፊነቱን ማስታወስ ከሁላችንም የሚጠበቅ ነው።
ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት፣ "In the End, we will remember not the words of our enemies, but the silence of our friends." በማለት በተራ በተራ ከምንወቃቀስ፤ ወዳጅነታችንን አጠንክረን አንዱ ሲያለቅስ አንዱ አይቶ እንዳላየ የሚሆንባትን ኢትዮጵያ እንቀይር።
ሰሞኑን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ወራት ውስጥ የተገደሉ፣ አካላቸው የጎደለ፣ እንዲሁም ንብረታቸው የወደመባቸው ፍትህ ያገኙ ዘንድ ተስፋ አደርጋለሁ። ሀዘን ላይ ለምንገኝ ሁሉ እግዚአብሄር መጽናናትን ይስጠን። 16/16
You can follow @AlemayehuGK.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.