✍️✍️የድል መንገዳችን እና መጪው የግብፅ ሚድያ አካሄድ
**********
በሰላም ሙሉጌታ ( @selam_mulugeta)

👉 የህዳሴው ግድብ የመጀመሪያ ውሃ ሙሌት መጠናቀቅ ግብፅ እርቃን አስቀርቷል፤ ይበልጥ በዲኘሎማሲ እና በሚዲያው መስክ።
1/18
2/18
የሃገሪቱ መንግስት በጥሞና አካሄዱን እንዲያጤን አስገድዶታል።

ከሰሞኑ የግብፅ የሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ስተዲስ (Egyptian Center for Strategic Studies) ያወጣው Deconstructing Ethiopian Media Discourse on GERD የሚለው ፅሁፍ . . .
3/18
. . በግድቡ ድርድር የሽንፈታቸው አንዱ እና ዋናው ምክኒያት በሚዲያው ግምባር ኢትዮጵያ የምታካሂደውን ዘመቻ መመከት አለመቻላቸው መሆኑን ማዕከሉ ገልጿል።
ይህም የግብፅን ሽንፈት እና የእኛን የድል መንገድ መስካሪ ያደርገዋል።
4/18
ሃተታው ከግድቡ ጋር ያለውን የኢትዮጵያን የሚድያ አጠቃቀም እና የዘገባ ጭብጦች ላይ አትኩሯል። ግብፅ የኢትዮጵያን ትርክት ፋርሽ ለማድረግ በቀጣይ ምትሄድበትን መንገድ አመልክቷል ።
5/18
ባለፋት አስር አመታት ይበልጥ ደግሞ ከሁለት አመት ወዲህ "ኢትዮጵያ ከምክኒያት እና እውነታ ይልቅ ስሜታዊነትን ማዕከል ያደረጉ የተቀናጀ የሚድያ ዘመቻን እያካሄደች ነው" ይላል። መደበኛ እና ማህበራዊ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም . . .
6/18
. . ዜጎችንና አለም አቀፍ ማህረሰብን መንግስት ከጎኑ ለማሰለፍ ሰርታለች ይላል።
የእስካሁኑ የኢትዮጵያ የሚዲያ ዘመቻ ሶስት ጭብጦች ላይ ያተኮረ ነው ይላል ፅሁፋ፦

1. የኢትዮጵያ ህዝብ በግድቡ ላይ የሚካሄደውን ድርድር ኢፍትሀዊ (Injustice) . . .
7/18
. . መሆኑን እንዲቀበል ማድረግ።
2. በአባይ ውሃ አጠቃቀም ኢትዮጵያን ተበዳይ/ተጎጂ አድርጎ ለአለም ማቅረብ።
3. ጉዳዩን የ"አረባዊት" ግብፅ እና የ"አፍሪካዊት" ኢትዮጵያ ውጥረት (Confrontation) ማስመሰል ናቸው።
8/18
👉**የማህበራዊ ዘመቻው ማዕበል**

"ኢትዮጵያ ለዘመቻዋ ብዙ አይነት የሚድያ አይነቶችን በስልት እየተጠቀመች ነው።
ይበልጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በታቀደ እና በተቀናጀ መንገድ በኢትዮጵያውያንና በመካከለኛው ምስራቅ ያሉ ወዳጆቻቸው በማደራጀት. .
9/18
. . የማህበራዊ ዘመቻን እያካሄዱ ነው። "ሃሰተኛ" ትርክቶችን እና የጥላቻ መልዕክቶችን እያሰራጩብን ይገኛሉ" ይላል ፅሁፋ። ዘመቻውን የግብፅን መንግስት ለመጫን፣ የአለም ማህበረሰብን ድጋፍ ለማግኘት እንዲሁም በውስጥ የህዝባቸውን ድጋፍ . . .
10/18
. . ለማግኘት የሚደረግ መንግስታዊ ስራ ነው ይለዋል።

የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሙሁራኖች በውስጥ ከሚሰሩት ስራ ባሻገር የኢትዮጵያን ዋና የሚዲያ ትርክት እና ጭብጦች ፋርሽ ማድረግ ቀጣዩ ዋናው ስራቸው እንደሚሆን ተገልጿል።
11/18
የግብፅ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ በቀጣይ በሁሉም የሚድያ አይነቶች ለሚያካሂደው ዘመቻ ቁልፍ ያላቸው **ሶስት አብይ ጭብጦች እንደሚከተሉት ናቸው፦

1. ኢትዮጵያ የምታሰራጨውን የመልዕክቶች ይዘት መለየት እንዲሁም የሃሰት እና . . .
12/18
. . ተቃርኖአዊ መረጃዎችን ተከታትሎ ማጋለጥ።
2. በግድቡ ጉዳይ ይፋዊ የኢትዮጵያ መንግስት ትርክትን መረዳት። በጉዳዩ ላይ ፅንፈኛ እና ለዘብተኛ አቋም ያላቸውን መለየት። ከዚህ አንፃር ዋና ዋና የማህበራዊ ሚዲያ ባለገፆችን . . .
13/18
. . መከታተል ትኩረት ይሰጠው ይላል ፤ ፀሀፊዎቹ የመንግስት አቋም አስተጋቢዎች በመሆናቸው።
3. ከዘገባዎቹ ጥሬ መረጃ ባሻገር ድምፀታቸውን (tone) እና ከሃገራዊ (ኢትዮጵያ) አዉድ (context) ጋር አስተሳስሮ መተንተን ላይ እንዲተኮር ያሳስባል ።
14/18
ምክኒያቱም የግድቡ ጉዳይ የኢትዮጵያ የውስጥ ፓለቲካ ነፀብራቅ ስለሆነ ይላል ፅሁፋ።
3. ከዘገባዎቹ ጥሬ መረጃ ባሻገር ድምፀታቸውን (tone) እና ከሃገራዊ (ኢትዮጵያ) አዉድ (context) ጋር አስተሳስሮ መተንተን ላይ እንዲተኮር ያሳስባል።
15/18
ስለዚህም የግብፅ ሴንተር ፎር ስትራቴጂክ ስተዲስ በቀጣይ ሳምንታት የኢትዮጵያን የሚድያ ትርክት እና ጭብጦች እግር በእግር በመከተል ለማክሰም የሚያስችሉ ጥናቶችን ማውጣት እንደሚጀምር ፅሁፋ ይገልፃል። ይህ እንግዲህ በሚድያው ግምባር . . .
16/18
. . የደረሰባቸውን ሽንፈት መቀልበሻ ስልት መሆኑ ነው።

📍ሲጠቃላል እንደ እኔ ፦

• ፅሁፋ በግድቡ ጉዳይ በሁሉም መስክ ያስመዘገብነውን ድል የመሰከረ ነው።
• የሚዲያ ስራችን የዲኘሎማሲው ድል የጀርባ አጥንት እንደሆነ።
17/18
• ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ እያካሄድን ያለነው ዘመቻ ደግሞ የሚድያው ዘርፍ አውታር መሆኑን።
• በቀጣይ በሁሉም መልኩ ከእስካሁኑ የበለጠ የተቀናጀ እና ቀጣይነት ያላዉ ስራን መስራት እንዳለብን።
18/18
• የማህበራዊ እና የመደበኛ ሚዲያዎቻችን ስራ ይበልጥ በስርአት እና በስልት መመራት እንደሚገባው።
• ሙሁራኖቻችን ህዝብን በተገኘው መንገድ ሁሉ የማንቃት ስራን አብዝተው ይስሩ።

አመሰግናለሁ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=3088300547871793&id=100000756346594&sfnsn=mo
You can follow @iyoba4u.
Tip: mention @twtextapp on a Twitter thread with the keyword “unroll” to get a link to it.

Latest Threads Unrolled:

By continuing to use the site, you are consenting to the use of cookies as explained in our Cookie Policy to improve your experience.